1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶክተር መረራ የዋስትና ጥያቄ

ዓርብ፣ መጋቢት 29 2009

ዶክተር መረራ ለችሎቱ ሰላማዊ ታጋይ መሆናቸውን አስታውቀው በፖለቲካ ምክንያት መታሰሬ ይታወቅ ሲሉ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2atOO
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

Beri AA ( Dr Mererra's appeal ) - MP3-Stereo

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዶክተር መረራ ጉዲና ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ይግባኝ ዛሬ ተመለከተ ። ዛሬ ከሰዓት በኋላ ጉዳዩን የተመለከተው ይኽው ችሎት ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ህግ ተላልፈዋል ተብለው የተከሰሱት ዶክተር መረራ ለችሎቱ ሰላማዊ ታጋይ መሆናቸውን አስታውቀው በፖለቲካ ምክንያት መታሰሬ ይታወቅ ሲሉ ተናግረዋል ። በሌላ በኩል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ነኛ ወንጀል ችሎት በበኩሉ በእነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ጆሀር መሐመድ የተመሰረተው ክስ በሌሉበት እንዲታይ መበየኑን  የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ